መዋጮ ያደርጋሉ
ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን አስቤዛ እናዘጋጃለን
ልገሳዎችን ለማህበረሰቡ አድርሰን እናሳውቅዎታለን

የኔሰው ሰዎች በቀናነት የሚያደርጉት አስተዋእፆ በምን መልክ ጥቅም ላይ ዋለ የሚለውን ጥያቄ በቀላሉ በሚመልስ መልኩ የተዘጋጀ ነው።
አንድ ነገር ባደርግ ደስ ይለኛል ለሚሉ ሁሉ ትርጉም ባለው መልክ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቀል ሆኖ የተሰራ፣ በባህላችን ያለውን የመረዳዳት መንፈስ ዘመን የሚያሻግር አገልግሎት ነው።

እንዴት ማገዝ እችላለሁ?

በአሁኑ ወቅት ይህን እንቅስቃሴ በተለያዩ ክልሎች በሃላፊነት ወስደው ሊያንቀሳቅሱ የሚችሉ ብዙ ቀና ልቦችን እንፈልጋለን። ድሬደዋ፣ መቀሌ፣ አዋሳ (ሃዋሳ)፣ ናዝሬት (አዳማ)፣ ባህር ዳር እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ላይ እንቅስቃሴውን ለማስፋት እየሰራን እንገኛለን። በራስ ተነሳሽነት ለሚቋቋሙ የክክልል ኮሚቴዎች የራሳቸው የሆነ ድረ ገፅ እንዲኖራቸው ከማገዝ ጀምሮ ሌሎች ድጋፎችን እናደርጋለን።

የየኔሰው የበጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ በአካባቢዎ ለመጀመር የሚያስፈልጉትን መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም አደረጃጀት ለማወቅ አናግሩን።


ያናግሩን